The Program's Unique Features Include:

  • Face-to-face instructions by experienced Lincoln University professors from the United States
  • Curriculum designed by Lincoln University-USA
  • Degress are awarded by Lincoln University-USA
  • Programs are fully accredited both in the USA & Ethiopia

ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን MBA & BA ዲግሪ ፕሮግራሞችን ላለፉት 9 አመታት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አሁን ደግሞ አድማሱን በማስፋት American Academy of Financial Management ጋር በመተባበር  Certified Credit Analyst ላይ ለአንድ ሳምንት (ከነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 .) የሚቆይ የአጭር ጊዜ ስልጠና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ከሌሎች ባንኮች እና ተጔዳኝ የሙያ ዘርፎች ለመጡ ከፍተኛ የሂሳብና ክሬዲት ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡

ተቋሙ ከሚሰጠው መደበኛ ትምህርት በተጔዳኝ  ከአሁን በፊት Stock Market (የካፒታል ገበያ) ላይ ተመሳሳይ ስልጠና የሰጠ መሆኑን አቶ አቤቱ መላኩ የዩንቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማት ባለሙያዎች የሚሳተፉበትና በካፒታል ወይም በስቶክ ገበያ አሠራር ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናትና ሥልጠና፣ ተቀማጭነቱ በአዲስ አበባ ከሆነው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በሚሠራው ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አስተባባሪነት መካሄድ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ዓውደ ጥናቱ ሥልጠናንም በማካተት ከነሐሴ 7 እስከ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚካሄድ የዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቶ አቤቱ መላኩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተዘጋጀው ዓውደ ጥናትና ሥልጠና ላይ ስለአክሲዮን ገበያ ገለጻ የሚያደርጉት ሚስተር ሰርጌይ አይቲያን (ዶ/ር) የተባሉና በዘርፉ ምርምር ያደረጉ ምሁር መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ሚስተር ሰርጌይ በካሊፎንሪያ ኦክላድ ውስጥ በሚገኘው የሊንከን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ የማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምና የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍሎች ዳይሬክተርም ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ በዩኒቨርሲቲው በሚገኘው የዘርፈ ብዙ ትምህርት መስኮች የምርምር ማዕከል ኃላፊ ስለመሆናቸውም ተገልጿል፡፡ ሚስተር ሰርጌይ፣ ‹‹Stock Market: Investment and Options›› በሚል ርዕስ መጽሐፍ ስለመጻፋቸውም ስለዓውደ ጥናቱ ከተሠራጨው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡  

አቶ አቤቱ እንደገለጹት ከሆነ፣ ዓውደ ጥናቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው በአሁኑ ወቅት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ እየተደረገ ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ የአክሲዮን ገበያ ምሥረታ አስፈላጊነት እየታመነበት በመምጣቱ ነው፡፡ በአፍሪካ ከሁሉም አገሮች በፊት ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ብትጀምርም፣ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ዓይነቱ ገበያ በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ፣ አገሪቱም ከሁሉ ኋላ ሆና መገኘቷ እንደሚያስቆጭ የሚገልጹት አቶ አቤቱ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህንን ገበያ ለመፍጠር እንቅስቃሴዎች በመታየታቸው፣ ቅድመ ዝግጅቶች ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ይረዳ ዘንድም በካፒታል ገበያ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናትና ሥልጠና በማካሄድ ሊመሠረት ስለሚችለው የካፒታል ገበያ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲቻል ለማገዝ ሲባል ዓውደ ጥናቱ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በመጀመርያው ቀን የዓውደ ጥናቱና የሥልጠናው መርሐ ግብር መሠረት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የካፒታል ገበያ የሚገኝበት ደረጃን የሚያሳይ ይዘት ያለው ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ይኽም የአክሲዮን ደላላ ድርጅቶች የአሠራር ሁኔታን የሚያሳይ ይሆናል፡፡ በሁለተኛው ቀን የአክሲዮን ግብይት፣ የጥሬ ገንዘብ የሒሳብ መዝገብ ሥርዓት በአክሲዮን ገበያ ውስጥ የሚስተናድበትን አሠራር የሚቃኝ መርሐ ግብር ተሰናድቷል፡፡

የካፒታል ገበያ ዓይነቶችና ባህሪያቸውን የተመለከቱ የሥልጠና ዓይነቶችም በዓውደ ጥናቱ መካተታቸው ታውቋል፡፡ የገንዘብ ዝውውር፣ የስቶክ ገበያ ማኔጅመንት፣ ቴክኒካል ትንተናን የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ ተብሏል፡፡ በዓውደ ጥናቱ ለኢንቨስትመንት ባንክ ባለሙያዎች፣ ለብድር ኃላፊዎች፣ ለአማካሪዎች፣ ለካፒታል ድርሻና ኢንቨስትመንት ተንታኞችና ለፋይናንስ አስተዳደር ተማሪዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መርሐ ግብር መዘጋጀቱን ፕሬዚዳንት አቤቱ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ በአገሪቱ እየታየ ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ ግዙፎቹን የአገሪቱ ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ፣ የስቶክ ገበያ በኢትዮጵያ የግድ መጀመር አለበት የሚለው ግፊት እየተበራከተ መጥቷል፡፡ የእነዚህ ኩባንያዎችን አክሲዮኖች በስቶክ ገበያ መሸጥ የሚያስችል አሠራር በመሆኑ፣ በስቶክ ገበያ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ተከታታይ መድረኮች ሊጎለብቱ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡  

Source: www.ethiopianreporter.com/

‹‹ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ማለት ሐሳብንና ገንዘብን አቀናጅቶ ሥራ መፍጠር ነው፡፡ ሰዎች እዚህ ተምረው ወጥተው እንዴት የራሳቸውን ሥራ መፍጠር እንደሚችሉ ነው የምናስተምረው፡፡ ሐሳብና ገንዘብ እንዴት እንደሚቀናጁ መንገድ እናሳያለን፡፡ ከፊዚቢሊቲ ጥናት አንስቶ ማርኬቲንግና ፋይናንሻል ስትራቴጂ እንዴት እንደሚቀረጽ እናስተምራለን፡፡ ምክንያቱም ያለ ፋይናንስ (ገንዘብ) ሐሳብ ብቻውን ውጤታማ አይሆንም፡፡ ድሮ በአገራችን ገንዘብ ያለው ሰው ነጋዴ፣ ነጋድራስ ይሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ሁኔታዎች ተለውጠዋል፡፡ ሐሳብ ሆኗል ገንዘብ፡፡ እነ ጎግል፣ እነ ፌስቡክ የሐሳብ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሐሳብ ነው ብር እየሆነ የመጣው፡፡ እኛ የምናስተምረው ሐሳብን ከገንዘብ ጋር አቀናጅቶ እንዴት ወደ ሥራ መተርጎም እንደሚቻል ነው፡፡‹‹በዚች አገር አንድ ሰው ሐሳብ ይዞ ሲነሳ፣ ብዙም ተቀባይነት የለውም፡፡ ባንኮች እንዴት ገንዘብ ሊያበድሩት እንደሚችሉ፣ ብር ያላቸው ሰዎች እንዴት ገንዘባቸውን ሊሰጡት እንደሚችሉ እንዲቀምር ነው የምናስተምረው፡፡ አገልግሎት ሰጪዎች ደግሞ እንዴት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ፣ ከአራትና አምስት ዓመት ገቢያቸው ጋር እንዲያስተያዩት፤ እንዴት የበለጠ ገቢ ማግኘት እንደሚችሉ፣ ገንዘባቸውን ባንክ ከሚያስቀምጡ ኢንቨስት ቢያደርጉ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙ ማሳመን መቻልን ነው የምናስተምረው ‹‹ከአንድ ቢዝነስ ወጥቶ እንዴት ሌላ የተሻለ ቢዝነስ መጀመር እንዳለበትም እናስተምራለን፡፡ ቀደም ሲል አያቱ ወይም አባቱ ቤንዚን ማደያ ካላቸው ልጃቸውም ቤንዚን ማደያ ነው የሚኖረው፡፡አሁን ግን ያ አይደለም ዘመናዊ ቢዝነስ፡፡ ቢዝነሱ በፊት ከነበረበት አድጎ ነው መገኘት ያለበት፤ ወደ ፈጠራ ነው መሸጋገር ያለበት፡፡ የቢዝነስ ሞዴል አስተዳደር ትምህርት ይህ ነው›› ብለዋል የዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንትና የኤምቢ ኤ ፕሮግራም ሥራ አስፈጻሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤቱ መላኩ፡፡ ከተመሰረተ አንድ መቶ ዓመት ሊሆነው ሁለት ዓመት ብቻ የቀረው የሊንከን ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባለፈው ሳምንት በሁለተኛ ዲግሪ በኤምቢኤ (Masters of Business Administration) ለ6ኛ ዙር፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን (ቢኤ) ዲግሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት እዚህ አዲስ አበባ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በድምቀት አስመርቋል፡፡ ለመሆኑ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እንዴት በአገራችን (Masters of Business Administration (ኤምቢኤ) ትምህርት መጀመር ቻለ? መቼ? መልሱን አቶ አቤቱ ይነግሩናል፡፡

ከተመሰረተ 98 ዓመታትን ያስቆጠረው፣ በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት ኦክላንድ ከተማ የሚገኘው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ በአራት ወይም በአምስት አገሮች በኤክስቴንሽን ያስተምራል፡፡ የአፍሪካ ተወካይ ናይጀሪያ ነበረች፡፡ ይህ ካምፓስ በፀጥታ ችግር መዘጋቱን አቶ አቤቱ በማስታወቂያ ሰሙ፡፡ እንዴት አፍሪካን የሚያህል አህጉር ያለ ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ይቀራል? በማለት ጠየቁ እኛ ለደህንነታችን ነው ቅድሚያ የምንሰጠው ተባሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ አፍሪካን እንድትወክል ተመኙና ኢትዮጵያስ? በማለት ጠየቁ በኢትዮጵያ ሰላም አለ? ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ በርካታ ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ድርጅቶች ያሉባት፣ ፈረንጆች በእኩለ ሌሊት የሚንሸራሸሩባት ናት በማለት መለሱ፡፡ “ለምን ፕሮፖዛል ጽፈህ ለባለ አደራ ቦርድ አቅርበህ አትሞክርም?” አሏቸው፡፡ ፕሮፖዛል ፅፈው አስገቡና ሰዎችም ረድተዋቸው ተቀባየነት አገኙ፡፡ የባለ አደራ ቦርዱ ሊቀ መንበር ግን ጥርጣሬ ገባቸው፡፡ ‹‹ይህ ሰው የተማረው ስለ ቢዝነስ ነው፡፡ የአካዳሚክ እውቀት የለውም፡፡ ታዲያ እንዴት ዩኒቨርሲቲውን መምራት ይችላል?” ሲሉ ጠየቁ፡፡ ቀደም ሲል አቶ አቤቱ ብሉናይል ኢንተርፕራይዝ  ኩባንያ አቋቁመው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ አምቦ ውሃንና በደሌ ቢራን ወደ አሜሪካ ወስደው ለ5 ዓመት የሸጡና ያስተዋወቁ ሰው ናቸው፡፡ እዚህ አገር ቤት በተፈጠረ ችግር ተቋረጠ እንጂ አምቦ ውሃው በአሜሪካ ገበያ ጥሩ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፡፡  ለባለአደራ ቦርዱ ሊቀመንበር ጥያቄ፣ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ፣ ‹‹ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ) ውሃ አምጥቶ በአሜሪካ ገበያ መሸጥ ከቻለ፣ ይህንን ዩኒቨርሲቲ አገር ቤት ወስዶ እንዴት ነው መምራት የሚያቅተው?” በማለት ተሟገቱላቸው፡፡ በዚህ ዓይነት በሊንከን ዩኒቨርሲቲ ተወክለው ወደ ኢትዮጵያ ተላኩ፡፡ ሊንከን ዩኒቨርሲቲ… እዚህ (ኢትዮጵያ) ሲመጣ ድንበር ተሻጋሪ ስለሚባል ትምህርት ግልጽ መመሪያ አልነበረም፡፡ ‹‹ጥርጣሬውም ስለነበር ሊፈቅዱልኝ አልፈለጉም ነበር፡፡ ሦስት ወር ሙሉ ከወዲያ ወዲህ በመመላለስ ጫማዬን ጨርሼ ምንም ውጤት ስላላገኘሁ፣ ከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ገብቶኝ ነበር›› ይላሉ አቶ አቤቱ ሊንከን ዩኒቨርሲቲን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ገጥሟቸው የነበረውን ችግር ሲያስታውሱ፡፡

በመጨረሻም  ተስፋ ቆርጠው ወደ አሜሪካ ለመመለስ ሲነሱ፣ ቀደም ሲል ያውቋቸው የነበሩትን ወዳጃቸውን፤ ‹‹ሰላም ሁን›› ለማለት ቢሮአቸው ደወሉላቸው፡፡ ወዳጃቸውም ‹መቼ መጣህ?›› በማለት ጠየቁ፡፡ አቶ አቤቱ ‹‹አይ፤ ሳላይህ ብሄድ ውቃቢህ ያየኛል ብዬ ነው የደወልኩት እንጂ መሄዴ ነው›› አሉ፡፡፡ ወዳጃቸውም ‹‹መቼ መጣህ›› አሉ፡፡ ‹‹ለዚህ ጉዳይ ነበር የመጣሁት፡፡ አሁን ስላልተሳካልኝ ተስፋ ቆርጨ መመለሴ ነው›› በማለት መለሱ፡፡ ‹‹ስልኩን ዝጋው፤ መጣሁ›› ብለው፤ አቶ አቤቱ ወደ ነበሩበት ሄደው በመኪና ወደ ቢሯቸው ወሰዷቸውቢሮ እንደደረሱ ለምን ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ፤ ያደረጉትን ጥረት፣ አልሳካ ቢላቸው ተስፋ ቆርጠው ለመመለስ እንደወሰኑ በዝርዝር አጫወቷቸው፡፡ ወዳጃቸው በሰሙት ነገር በጣም ተገረሙ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የሚያውቋቸው ሰዎች ስለነበሩም እነሱን በስልክ አግኝተው ስለጉዳዩ አጫወቷቸውና፤ ‹‹እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ይታለፋል? ያገር ጉዳይ’ኮ ነው›› በማለት ፋክስ አደረጉላቸው፡፡ ከዚያም አሪጂናል ዶክመንቶችን አገላብጠው ተመለከቱ፡፡ ‹‹ ይህን ይዘህ ማን ጋር ሞከርክ?›› በማለት ጠየቋቸውየ‹‹እገሌ የሚባል ያልሞከርኩበት ባለሥልጣን የለም፡፡ በማለት መለሱ፡፡ ‹‹ለምን አንድ ሦስት ቀን አትቆይም?›› አላቸው፡፡ አቶ አቤቱም፤ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ አያልቅም፡፡ ስለዚህ ተመልሼ መስራት አለብኝ፡፡ በጊዜ አልቀልድም፣ ስለ ጊዜ አጠቃቀም ነው የተማርኩት›› አላቸው  ሰዎቹም፤ ‹‹ግድ የለም፤ ተስፋ አትቁረጥ፤ እኛም እንረዳሃለን››አሏቸው፡፡ በዚህ ዓይነት ከሚመለከታቸው ቢሮዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር ተጀምሮ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡ ፈቃዱን ሲያገኙም ብቻቸውን እንዲሠሩ ሳይሆን፣ አስተማማኝነቱ ከተረጋገጠ ተቋም ጋር ተዳብለው እንዲሰሩ ከኒው ጀኔሬሽን ዩነቨርሰቲ ኮሌጅ ጋር ተዳብለው በ2010 መሥራት ጀመሩ፡፡

ለአንድ ዓመት ከሰሩ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ከኮሌጁ ጋር ተዳብሎ መስራቱን አስተዳደሩም ሆነ ተማሪዎች ስላልወደዱት፣ እንደገና አመልክተው ፈቃድ ስላገኙ ነፃ ሆነው በራሳቸው መስራት መጀመራቸውን አቶ አቤቱ አስረድተዋል፡፡  ዩኒቨርሲቲውን ለመክፈት ግን በጣም ፈታኝ ችግሮች ገጥሟቸው እንደነበር አቶ አቤቱ ይናገራሉ፡፡ ተስፋ ቆርጠው ሊመለሱ ሲነሱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በነበሩ ሰዎች ድጋፍ አግኝቶ (እ.ኤ.አ)፣ በ2010 ከኒውጀኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ጋር ተዳብሎ እንዲሠራ ፈቃድ እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚያስተምረው ስለቢዝነስ ነው፡፡ ዘመናዊ የቢዝነስ ጥበብ አስተምሮ በማስተርስ (ሁለተኛ) ዲግሪ ያስመርቃል፡፡ ዘንድሮ ግን ለማስተርስ ፕሮግራም ሥልጠና ብቁ የሆኑና ተገቢውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎችን ለመመልመል ያስችለው ዘንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አስተምሮ 18 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል፡፡ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ፣ በዲያግኖስቲክ ኢ-ሜጂንግ (ስካኒንግ፣ ሲኖግራፊ፣) ስፔሻላይዝድ ያደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ዓመት በዚህ እውቀት አስተምሮ በመጀመሪያ ዲግሪ ለማስመረቅ አቅዷል፡፡ ነገር ግን አንድ ችግር አለበት፡፡ ይኼውም ተማሪዎች ወጥተው ልምምድ የሚያደርጉበት ሆስፒታል ያስፈልጋል ሁለተኛ፣ ለሆስፒታሉ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች መግባት አለባቸው፡፡ መሳሪያዎቹን ለማስገባት የጉምሩክ ፈቃድ ይፈልጋል፡፡ ፈቃዱን ለማግኘት ደግሞ ዕቃዎች መሟላት አለባቸው የሚል ችግር ቢያጋጥማቸውም ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የእኛ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ኳሊቲው (ጥራቱ) የትምህርት አሰጣጡ ካሪኩሌም የሚቀረፀው በ1919 ዓ.ም በተመሠረተውና ዕድሜ ጠገብ በሆነው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ነው ያሉት አቶ አቤቱ፣ ከሚያስተምራቸው 11 ኮርሶች ስምንቱን መምህራን ከአሜሪካ ሊንከን ዩኒቨርሲቲ መጥተው እንደሚያስተምሩ፣ ሦስት ኮርሶች ብቻ እዚህ ባሉ መምህራን እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ እኛ የምንደራደረው በጥራትና ጥራት ብቻ ነው፡፡ የምናስተምራቸውን ጥቂት ሰዎች በጥራት አውጥተን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እናደርጋለን ዩኒቨርሲቲው በትምህርት መረጃ መጻሕፍት የተሟላ መሆኑን አቶአቤቱ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ ቤተ መጽሐፍት የተጀመረው በእኛ ዩኒቨርሲቲን ነው፡፡ ዳታ ቤዙ አሜሪካ ሆኖ ተማሪዎች እዚህ ተቀምጠው የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍት ነው የሚጠቀሙት፡፡ መጽሔትና ጋዜጦችን  ጨምሮ የበርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍት መጠቀም ይችላሉ፡፡

ከአሜሪካ የሚመጡ መምህራን በኢንተርኔት ከራሳቸው መጻሕፍት ነው የሚያስተምሩት፡፡ የእኛ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ለየት ያሉ ናቸው፡፡ ትምህርታቸው እንደዚህ አገር መምህራን በንድፈ ሐሳብ (ቲዮሪ) ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ቢዝነስ ላይ ያሉና ሕይወታቸውን እየኖሩበት ያለውን ልምድ ነው የሚያስተምሩት፡፡ ለምሳሌ በምረቃው ላይ የተገኙት የባለአደራ ቦርዱ ሊቀመንበር የህክምና ዶክተር (አንኮሎጂ- የካንሰር ስፔሻሊስት) ናቸው። ነገር ግን እዚህ ሲመጡ የሚያስተምሩት የ200 ሆስፒታሎች ኃላፊ ስለሆኑ ሊደርሺፕና ኮሙኒኬሽን ነው››  በማለት አብራርተዋል፡፡  ለአንድ አገር እድገትና ለውጥ ትምህርት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ቁጥር ሳይሆን በጥራት ሲሰጥ ነው የተፈለገው ራዕይ እውን የሚሆነው ይላሉ - አቶ አቤቱ፡፡ ‹‹ የእኛ የወደፊት ዕቅድ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ሁለተኛ ዲግሪና ዶክትሬት ድረስ ከስር መሰረቱ ኮትኩቶ ማውጣት ነው፡፡ የእኛ ዕቅድ እንደ ሀርቫርድና እንደ ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ከሥር ከመሰረቱ ኮትኩቶ ማውጣት ነው፡፡ ፐሮፖዛል አስገብተን የመሬት ጥያቄም አቅርበናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ከአሜሪካ- ሳንፍራንስኪስኮ ከሪችሞንድ ከተማ ሳንቴ የተባለ ሬስቶራንት ባለቤት ወ/ሮ መንበረ አክሊሉ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኃላፊዎች ጋባዥነት ተገኝታ፣ የስኬት ታሪኳን ለተመራቂዎች ተናግራለች፡፡ በሌላ በኩል ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ተሰማርተው ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉት ለአቶ ብዙአየሁ ታደለ፣ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል፡፡ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ባሳለፋቸው ስድስት ዓመታት ብዙ ችግሮችን ቢያጋጥሙትም ዋናው ችግር ቢሮ ክራሲው መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ኤጀንሲ የሚባለው ድርጅት ገምጋሚ ብቻ ሳይሆን ተገምጋሚም ነው ለእኔ፡፡ በድንገት መጥተው የሚጠይቁት የዛሬ 30 እና 40 ዓመት የሚሠራበትን ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ በዋይ ፋይ ዘመን ላይ እያለን፣ የግድ ገመድ ያለው ኮምፒዩተር ማሳየት የለብንም፡፡ ኔትወርኩ የታለ? በማለት ይጠይቃሉ›› ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀው ክፍያ ወደድ እንደሚል አቶ አቤቱ ያምናሉ፡፡ ‹‹እኛ የምናስተምረው የርቀት (non-distance) አይደለም፡፡ በክፍል ውስጥ ከተማሪዎች ጋር ፊት ለፊት (non-Distance) ነው፡፡ ስለዚህ መምህራኑ ከአሜሪካ ሲመጡ የአውሮፕላን ይከፈላል፣ ክፍል ገብተው የሚያስተምሩበት የአበል ብቻ 1400-1500 ብር ይከፈላቸዋል፡፡ ሌላው ክፍያውን የሚያንረው የማስተማሪያ ሕንፃው ኪራይ ነው፡፡ ለሕንፃው ኪራይ የሚከፈለው 85 ሺ ብር ቢቀር፣ በእርግጠኝነት የተማሪዎች ክፍያ ይቀንሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር ተግዝቦ ሕንፃ መሥሪያ ቦታ ቢሰጠን፣ ወደፊት የተማሪዎች ቁጥር ስለሚጨምር፣ የትምህርት ክፍያውም ይቀንሳል›› በማለት አስረድተዋል፡፡

Source: www.addisadmassnews.com

ከአሜሪካው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የሚሠራው ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ በኢትዮጵያ ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ድኅረ ምረቃ ባሉት ዕርከኖች የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥባቸውን መርሐ ግብሮች ነድፎ ወደ ተግባር ለመግባት እየተዘጋጀ እንደሚገኝና ለዚህም የ37.5 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቅዳሜ፣ ታኅሳስ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሰባተኛ ጊዜ ተማሪዎችን ባስመረቀበት ፕሮግራም ወቅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የትምህርት  አገልግሎቱን ለማስፋፋት የቀረፀውን ፕሮግራም በአዲስ አበባና በባህርዳር በሙከራ ደረጃ እንደሚጀምር ገልጿል፡፡ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ድኅረ ምረቃ ድረስ የሚዘልቀውን ፕሮጀክት ለመተግበር በዋና ዋና ከተሞች ግንባታ ለማካሄድ የመሬት ጥያቄ ማቅረቡን የገለጹት የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት አቶ አቤቱ መላኩ፣ ለዚህ ፕሮጀክት የሚውለውን ገንዘብ ለማግኘት ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

እንደ አቶ አቤቱ ገለጻ፣ ተቋሙ አገልግሎቱን ለማስፋትና ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን ፋይናንስ ኦቨርሲስ ፕሮጀክት ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን (ኦፒክ) ከተባለ ተቋም በሚገኝ ብድር ፕሮጀክቱን ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ጭምር ይንቀሳቀሳል የተባለው ይህ የትምህርት ተቋም፣ የአሜሪካ ዜጎች በተለያዩ አገሮች ውስጥ በትምህርት፣ በእርሻ፣ በጤናና በመሳሰሉት መስኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉም በዝቅተኛ ወለድ ብድር የማመቻቸት ሥራ የሚሠራ ተቋም እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በካሊፎርኒያ ከሚገኘው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እየሠራ በመሆኑ፣ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቡን  አመልክተዋል፡፡ የብድር ጥያቄው አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኝና ፕሮጀክቱንም በአፋጣኝ ወደ ሥራ ያስገባል የሚል እምነት እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ ይናገራሉ፡፡

ይህ ካልተሳካም ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ፕሮጀክቱን ተግባራዊ እናደርጋለን ያሉት አቶ አቤቱ፣ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ጥራት ላይ የተመሠረተ አገልግሎቱን በሌሎች ዘርፎችም መስጠቱን እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰባተኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ሥርዓተ ትምህርቱ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን ያገናዘበ የትምህርት አሰጣጥ እንደሚከተል ተጠቅሷል፡፡

የማስተማሪያ መርጃ መሣሪያዎችና የመማርያ መጻሕፍት በሊንከን ዩኒቨርሲቲ የሚቀርቡለት ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲው ቤተ መጻሕፍት አማካይነት ከ150 ሺሕ በላይ መጻሕፍትና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አጋዥ ማቴሪያሎችን ለማንበብም በሚያስችል ደረጃ የሚቀርቡበት ሲሆን፣ በአዲሱ ፕሮጀክት መሠረት ጥራት ላይ ያተኮረ ትምህርት ለመስጠት የሚረዱ ሥራዎችም እንደተካተቱ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ተቋሙ ተልዕኮ በሥራ ጫና ምክንያት የመማር ዕድል ማግኘት ላልቻሉ ሆኖም የትምህርት ሚኒስቴርን መመዘኛዎች ለሚያሟሉ ዕጩ ተማሪዎች ልዩ የማስተማሪያ መርሐ ግብር መንደፉም ተብራርቷል፡፡

ተቋሙ ተማሪዎቹን የኢንተርፕሪነርሺፕ አስተሳሰብና ክህሎትን እንዲላበሱ ከማድረግ ጀምሮ የሚሠሯቸው ጥናታዊ ጽሑፎችም በኢትዮጵያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጭብጦች ላይ ያተኮሩ፣ በተግባር የሚተረጎም መፍትሔ ጠቋሚ ሐሳቦችን እንዲያቀርቡ ማበረታታት ዓላማው እንደሆነ ተቋሙ ይገልጻል፡፡ ዕጩ ተማሪዎቹን ከጥናት እስከ ተግባር ባለው ሒደት ውስጥ ድረስ የቢዝነስ ዕቅድ በመቅረፅ የሚሳታፉበትን አሠራር ዘርግቷል፡፡ በተጨማሪም ምሩቃን ተማሪዎች በወደፊቱ ሕይወታቸው በትምህርት ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር የሚያሳዩበት መሠረት እንዲኖራቸው የሚያግዝ አካሄድ መቅረፁን አስታውቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በማስትሬት ዲግሪ ሥልጠና የሚሳተፉ ተማሪዎችን መቀበል የጀመረ ሲሆን፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ለመጀመርያ ዲግሪ የሚያስፈልገውን ሥርዓተ ትምህርት ከሊንከን ዩኒቨርሲቲ ሥርዓተ ትምህርት ጋር በማጣጣም የቀረፀው ሥርዓተ ትምህርት ፀድቆ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

በ2004 ዓ.ም. ተቋቁሞ ከሊንክን ዩኒቨርሲቲ ጋር እየሠራ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አገልግሎት በማስፋት በቅርቡ በጤና ሳይንስ መስክ (ዲያግኖስቲክ ኢሜጂንግ) የመጀመርያ ዲግሪ ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከሊንክን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ላለፉት ተከታታይ ስድስት ዙሮች በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን መስክ በማትሬት ደረጃ 172 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምረቃም 23 ተማሪዎችን በዚሁ መስክ፣ 14 ተማሪዎችን በመጀመርያ ዲግሪ ለማስመረቅ በቅቷል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚካኤል አርተር ሬይነር፣ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሊቀመንበር ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ የመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል (ዶ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓቱን አከናውነዋል፡፡ ዘንድሮ ከተመረቁት መካከል የቀድሞው የፍትሕ ሚኒስትር አቶ ብርሃን ኃይሉ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የሊንክን ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ባለቤት ለአቶ ብዙዓየሁ ታደለ የመጀመርያውን የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

Source: www.ethiopianreporter.com/

ስለኩባንያዎቻቸው እንቅስቃሴ እንጂ ኩባንያቹን በባለቤትነት ስለመምራታቸው ብዙም ሲናገሩ ከማይደመጡ ባለሀብቶች መካከል አቶ ብዙአየሁ ታደለ አንዱ ሆነው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ከ35 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የተለያዩ የንግድ ሥራ ዘርፎችን በመፍጠር እየሠሩ የሚገኙት አቶ ብዙአየሁ፣ ከእሳቸውና ካሏቸው ድርጅቶች ብዛት ይልቅ የፈጠሯቸው ኩባንያዎች ማንነት ጎልተው ሲነገርላቸው ቆይተዋል፡፡ አቶ ብዙአየሁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከእሳቸው ስምና ማምነት የተሻለ ቢታወቅ ውጤት ሊኖረው የሚችለው ቢዝነሱ በመሆኑ፣ ስለራሳቸው ከመግለጽ መቆጠብን ይመርጣሉ፡፡

የጎልማሳ ዕድሜ ያስቆጠረው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው በጋራም በተናጠልም ከ30 በላይ ኩባንያዎችን እንዲፈጥሩ አስችሏቸዋል፡፡ ይህን ያህል ኩባንያ የፈጠሩት እኝህ ሰው፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብም ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ ከቤተሰቦቻቸው ባገኙት ውርስ የቢዝነሱን ዓለም የተቀላቀሉት አቶ ብዙአየሁ፣ የመጀመርያ ሥራቸው ወላጆቻው ይታወቁበት የነበረውን አነስተኛ የቡና ንግድ  ሥራ  በመጀመር ነበር፡፡ ከ35 ዓመታት በፊት ወደ ቡና ንግድ ሲገቡ ሦስት ሠራተኞችን ይዘው ሲሆን፣ ዛሬ ላይ የፈጠሯቸው በርካታ ኩባንያዎች ከ6,000 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል አስገኝተዋል፡፡ ለዓመታት ስለገነቡት የቢዝነስ መጠንና ትልቅነት ይህ ነው በሚባል ደረጃ ሲገልጹ አልታዩም፡፡